ፓስፖርት ለማመልከት

1. አገልግሎቱ ያለቀ ፓስፖርት ለመቀየር/ለማደስ.
2. በወላጆቻቸው ፓስፖርት ተለጥፈው ሲጓዙ ለነበሩ ህጻናት.

1. አገልግሎቱ ያለቀ ፓስፖርት ለመቀየር/ለማደስ መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

* 4 የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት).
* ለመቀየር ወይም ለማደስ የተፈለገው ዋናው ፓስፖርት ማቅረብ.
* ለመቀየር ወይም ለማደስ የተፈለገው ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና * ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ በሁለት ኮፒ ማቅረብ
* የአገልግሎት ክፍያ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ የባንክ የክፍያ ደረሰኝ መሆን ይኖርበታል፡፡ ~Download Pdf

* የጣት አሻራ ማቅርብ ለሚጠበቅባችሁ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውንማቅረብ/መላክ. ~Download Pdf

* መጠየቂያ ቅጽ በሁለት ኮፒ መሙላት. ~Download Pdf

2. በወላጆቻቸው ፓስፖርት ተለጥፈው ሲጓዙ ለነበሩ ህጻናት መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

* 4 የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት).
* ከወላጆቻቸው ጋር የተጓዙበትን ፓስፖርት በሁለት ኮፒ.
* የአገልግሎት ክፍያ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ የባንክ የክፍያ ደረሰኝ መሆን ይኖርበታል፡፡ ~Download Pdf

* የጣት አሻራ ማቅርብ ለሚጠበቅባችሁ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውንማቅረብ/መላክ. ~Download Pdf

* መጠየቂያ ቅጽ በሁለት ኮፒ መሙላት. ~Download Pdf

* ለፓስፖርት አሻራ መሟላት ያለበት ~Download Pdf