በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን "ለሀገራችን ሉዓላዊነትና አንድነት ከመንግስታችን ጎን እንቆማለን" በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ አደረጉ!


በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን "ለሀገራችን ሉዓላዊነትና አንድነት ከመንግስታችን ጎን እንቆማለን" በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ አደረጉ!

በሺዎች የሚቆጠሩ በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን "ለሀገራችን ሉዓላዊነትና አንድነት ከመንግስታችን ጎን እንቆማለን" በሚል መሪ ቃል መንግስት በትግራይ ክልል የወሰደውን ህግ የማስከበር እርምጃ በመደገፍ እና በአንዳንድ የውጭ አካላት የሚደረገውን ያልተገባ ዲፕሎማሲያዊ ጫና በመቃወም መጋቢት 10 ቀን 2013 አ ም ሰልፍ አካሂደዋል፡፡

በካርቱም የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማዕከል በተካሄደው በዚህ ደማቅ ሰልፍ የሐይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ሴቶች እና ወጣቶች ተሳትፈዋል።
ሰልፈኞቹ በፕሮግራሙ ማብቂያ ባወጡት ባለ ስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ አክራሪው የህወሓት ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ የፈፀመውን አጸያፊ ጥቃት እና የሀገር ክህደት ወንጀል አውግዘዋል፡፡ ጥቃቱን ተከትሎ መንግስት የወሰደው አፋጣኝ ህግ የማስከበር እርምጃ ሀገርን ከመበተን እንደታደገ እና ህግ ከማስከበር ውጭ ሌላ አማራጭ እንዳልነበረም ገልጸዋል።
በአንዳንድ የህውሓት ርዝራዦች እና ደጋፊዎች እየተካሄደ ያለውን የሐሰት መረጃ ስርጭት እና ፕሮፓጋንዳ እንዲሁም በአንዳንድ ሀገራት እና ድርጅቶች እየተሞከረ ያለውን ጫናም አውግዘዋል።
መንግስት ከህግ ማስከበሩ ጎን ለጎን በክልሉ በህወሓት የወደሙ የመሰረተ ልማቶችን በመጠገን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የወሰደውን እርምጃ እና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ንጹሐን ዜጌች ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ የወሰደውን እርምጃም አድንቀዋል።
በሰልፉ ላይ ንግግር ያደረጉት በሱዳን የኢፌዴሪ ባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በበኩላቸው ኢትዮጵያውያኑ ለሀገራቸው አንድነት ከመንግስታቸው ጎን በመቆም ያደረጉትን ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ አድንቀው፣ ትህነግ ለውጡን ተከትሎ የበላይነቱን በማጣቱ ብቻ ሀገርን ለመበተን ክህደት መፈጸሙን ገልፀዋል።
ይህ ቡድን ከዓነሳሱ ጀምሮ ትግራይን ገንጥሎ ነፃ አገር ለመመስረት ያለመ አገራዊ ራእይ የሌለው ጠባብ ቡድን መሆኑን አምባሳደሩ በመጥቀስ ተሳክቶለት ቢሆን ኖሮ በሀገራችን እና በቀጠናው ሊፈጠር ይችል የነበረውን አደጋ እጅግ የከፋ እንደነበር ገልፀው፣ ሆኖም በመሪዎቻችን ብልሃትና በሰራዊታችን ጥንካሬ በአጭር ጊዜ ሴራው ሊከሽፍ እንደቻለ አውስተዋል።
በሌላ በኩል ህግ የማስከበሩን ተግባር በብቃት ብንወጣም የትህነግ እርዝራዦች፣ ተከፋዮቻቸው እና አንዳንድ አካላት በትህነግ ላይ ነፋስ ለመዝራት በአገራችን ላይ ያልተገባ ጫና በማድረግ ላይ እንደሙገኙ አምባሳደሩ ገልፀው፣ ሁሉም ዜጋ ለሀገሩ ዘብ መቆም እንደሚገባውና በመገናኛ ብዙሀን የሚሰራጩ የሐሰት መረጃዎችን እና ፕሮፖጋንዳ ለማክሸፋ ተግቶ እንዲሰራ አሳስበዋል።

Back to Home

More News ..

የሱዳን ምሁራን የልዑካን ቡድን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ Read More


በሱዳን ለምትገኙ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ! Read More


Prime Minister’s Office Press Briefing – 15 June 2021 Read More


Statement on the Resolution of the League of Arab States on the GERD Read More


The ministry of foreign affairs of Ethiopia biweekly press briefing Read More


Press Release: On the Media and alleged human rights violations and other crimes committed in #Tigray Read More


Press Release: On G7 Foreign Ministers' Statement on the situation in Tigray Read More


በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን "ለሀገራችን ሉዓላዊነትና አንድነት ከመንግስታችን ጎን እንቆማለን" በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ አደረጉ! Read More


Press Statement on the Latest Situation in the #Tigray Region Read More


"Held a review meeting with the #Tigray Region SOE Taskforce and the Provisional Administration Read More


Read More News...

VISITOR COUNT
TODAY COUNT:   30
THIS WEEK:   587
THIS MONTH:   587
THIS YEAR:   20462
TOTAL:    20462
         Services
      * Visa Service
      * Document Authentication
      * For Diplomatic Community
      * For Bussiness Community
      * Government E-Services
         Media
      * Week in the Horn
      * Press Release
      * Speech
      * Articles

Subscribe Our News Posts